የ2022 የእርስዎ ድምጽ ዋጋ አለው (YVM) የዳሰሳ ጥናት ለተማሪዎች እና ሰራተኞች በማርች 7፣ እንዲሁም ለቤተሰቦች በማርች 14 ይከፈታል። APS እና የአርሊንግተን ለልጆች፣ ወጣቶች እና ቤተሰቦች አጋርነት(APCYF) የጋራ ጠቀሜታ ያላቸውን ቦታዎች መረጃ ለመሰብሰብ እና የወጣቶችን እና የቤተሰብ ደህንነትን በጥልቀት ለመረዳት በየሁለት አመቱ የ YVM ዳሰሳ ያካሂዳሉ። ርእሶቹ ደህንነትን (የትምህርት ቤት እና የማህበረሰብ ሁኔታ)፣ ጤና እና ደህና መሆንን፣ ድምጽን እና ተሳትፎን ያካትታሉ። የጊዜ ሰሌዳ እና የዳሰሳ ጥናት አስተዳደር
- ሰራተኞች እና ተማሪዎች (ከ4-12ኛ ክፍል) – ማርች 7 – ኤፕሪል 10
- ቤተሰቦች – ማርች 14 – አፕሪል 10
የተማሪው የዳሰሳ ጥናት የሚካሄደው በመማሪያ ክፍል ውስጥ ሲሆን የሚጠናቀቀው በመስመር ላይ ነው። ወላጆች የኢሜል ግብዣ ይደርሳቸዋል ወይም ኢሜል መዝገብ ላይ ከሌለ፣ የዳሰሳ ጥናቱን ከበይነመረቡ ጋር ከተገናኘ ከማንኛውም መሳሪያ ላይ ስለማግኘት መመሪያዎችን በፖስታ ይደርሳቸዋል። የ APS ሰራተኞች ሚስጥራዊ የዳሰሳ ጥናቱን በመስመር ላይ እንዲያጠናቅቁ ኢሜል ይደርሳቸዋል።የዳሰሳ ጥናቱ አስተዳደር ሒደት የሚካሄደው እራሱን የቻለ የትምህርት ዳሰሳ ጥናት ምርምር ኩባንያ በሆነው ፓኖራማ ኢዱኬሽን ነው። ውጤቶቹ ሚስጥራዊ ሲሆኑ በሁለቱም የትምህርት ቤት ክፍል እና አውራጃ ውስጥ የሚሰሩ ስራዎችን ለማሳወቅ ይጠቅማሉ። መረጃው በተጨማሪም በ2018-24 ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መሻሻልን ለመለካት አዲስ መመዘኛዎችን ለ APS ይሰጣል።ስለ YVM፣ ተደጋጋሚ ጥያቄና መልሶችን ጨምሮ፣ ናሙና የዳሰሳ ጥናቶች እንዲሁም ቀደምት የYVM የዳሰሳ ጥናቶች ውጤቶች ተጨማሪ መረጃዎች በ APS ድርጣቢያ ላይ ይገኛል።