ውድ APS ቤተሰቦች፣
የበዓል ቅዳሜና እሁድን እንደወደዱት እና ዘና ለማለት እና ለማክበር ጊዜ እንዳገኙ ተስፋ አደርጋለሁ። ለ2020-2021 የትምህርት ዓመት ለመዘጋጀት ሥራችን በበጋው ወቅት በሙሉ ይቀጥላል እናም እርስዎ ለማሳወቅ በየሳምንቱ ማክሰኞ አንድ መሻሻል ማጋራቴን እቀጥላለሁ።
ትናንት ሀምሌ 6 ለተማሪ(ዎች) በተሻለ ሁኔታ የሚሰራውን የትምህርት አሰጣጥ ሞዴልን እስከ ሀምሌ 20 ድረስ ለመምረጥ ለ APS ቤተሰቦች በ ParentVUE ውስጥ የምርጫ ሂደቱን ጀምረናል። ሁለቱ ምርጫዎች የአካል/የርቀት ቅይጥ ትምህርት ወይም የሙሉ ጊዜ የርቀት ትምህርት ናቸው። ስለዚያ ሂደት የሚያስጠነቅቅዎ የትምህርት ቤት ንግግር ኢሜል እና የጽሑፍ መልእክቶች ሊደርሰዎ ይገባል እና ተጨማሪ ዝርዝር መመሪያዎች በ APS website ላይ ይገኛሉ።
ያስታውሱ ወደ ParentVUE ሲገቡ እና ወደ “Student Information” (የተማሪ መረጃ) ትር ሲሄዱ፣ “Edit Information” (መረጃ አርትዕ) የሚለውን መምረጥ እና ለእያንዳንዱ ተማሪ የትምህርት እና የትራንስፖርት ምርጫን በተመለከተ በቀይ ያለውን መረጃ ለማዘመን ወደ ታች መሸብለል አለብዎት። ለመግባት ወይም ParentVUE ለመድረስ ችግር ከገጠምዎ የትምህርት ቤትዎ ዋና ቢሮ ሊረዳዎት ይችላል ወይም ደግሞ ድህረገጽ ላይ የሚገኙ መላ ፍለጋ ጠቃሚ ምክሮችን መሞከር ይችላሉ። ወደ ትምህርት ቤትዎ ደውለው እና ከስምዎ እና ከስልክ ቁጥርዎ ጋር መልዕክት ካስቀመጡ አንድ የሰራተኛ አባል ወደ እርስዎ ይመለሳል። ለበልግ እቅድ ለማቀድ የእርስዎ ምላሽ በጣም አስፈላጊ ነው ስለሆነም እባክዎን ምርጫዎችዎን እስከ ሀምሌ 20 ድረስ ያጋሩን። ምላሽዎ በ 20 ካልደረሰን ተማሪዎ(ችዎ) በቅይጡ ሞዴል ይመዘገባሉ።
በ engage@apsva.us ኢሜይል አማካይነት ከፍተኛ የጥያቄዎችን መጠን መቀበሉን ቀጥለናል እናም በተቻለን ፍጥነት ምላሽ እየሰጠን ነው። እየደረሱን ባሉ ጥያቄዎች ላይ በመመርኮዝ ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና ትምህርታዊ ሞዴል ገጾች በየቀኑ ስለሚሻሻሉ እባክዎን አዲስ ጥያቄ ወደ እኛ ከመላክዎ በፊት ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎችን በድህረገጹ ላይ ይመልከቱ። የተለዩ የኮርስ አቅርቦቶችን እና የጊዜ ሰሌዳዎችን የሚመለከቱ አንዳንድ ጥያቄዎች በዚህ ጊዜ ሊመለሱ አይችሉም ምክንያቱም እነዚያ ውሳኔዎች የሚደረጉት በተማሪ ምዝገባ እና በሠራተኞች አተክሮቶች ላይ በመመርኮዝ ነው።
ስለ APS ወደ-ትምህርት-ቤት-መመለስ እቅድ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚቀጥለው ማክሰኞ ሐምሌ 14 ቀን ከምሽቱ 6፡30 እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ምናባዊ የማህበረሰብ ከተማ አዳራሽ ዝግጅት አስተናግዳለሁ። የትምህርት ቤት ቦርድ ሊቀመንበር ሞኒክ ኦግራዲይ እና ለማስተማር እና ለመማር ምክትል የበላይ ተቆጣጣሪ ብሪጄት ሎፍት ይቀላቀሉኛል። የከተማው አዳራሽ ዝግጅቱ በ Microsoft Teams እና በፌስቡክ ቀጥታ ስርጭት በ Arlington Public Schools የፌስቡክ ገጽ ላይ ይሰራጫል። ይህንን ቀን እንዲያስቀምጡ አበረታታዎታለሁ እናም በዚህ ሳምንት ወደ መጨረሻ School Talk (በት/ቤት ንግግር) አማካይነት በተመሳሳይ ጊዜ ትርጓሜዎችን ማግኘት እንዴት እንደሚቻል ተጨማሪ ዝርዝሮችን እናጋራለን።
እስከዚያ ድረስ ቅዳሜና እሁድ በደረሱ ጥያቄዎች ላይ በመመርኮዝ አንፅኦት ለመስጠት የምፈልጉባቸው ጥቂት ነጥቦች አሉ፡
- APS የሙሉ ጊዜ የትምህርት ቤት ወስጥ አማራጭን የማይሰጥበት ምክንያት፡ ከሁለቱም ሞዴሎች ጋር መደረግ የሚኖርባቸው ከባድ ውሳኔዎች መኖራቸውን እንገነዘባለን። በCDC፣ በቨርጂኒያ የጤና ክፍል እና በአከባቢው የጤና ባለሥልጣናት በተሰጡት የአካላዊ መራራቅ መስፈርቶችን ምክንያት በዚህ ጊዜ የሙሉ ጊዜ የትምህርት ቤት ወስጥ ሁኔታ አይቻልም። የአካላዊ መራራቅ በማንኛውም አንድ ጊዜ በትምህርት ቤት ውስጥ ሊኖር የሚችሉትን ተማሪዎች እና ሰራተኞች ብዛት ይገድባል ስለሆነም ቅይጥ ሞዴሉ በመማሪያ ክፍል እና በአውቶቡሶች ወስጥ ያሉ አቅሞችን ለመቀነስ ግማሽ የሚያህሉ ተማሪዎች ከሳምንቱ የተወሰነውን በትምህርት ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ያስችላቸዋል።
- የጤና ሁኔታዎች ቢሻሻሉ APS ምን ያደርጋል፡ የጤና ሁኔታዎች ከተሻሻሉ እና የአካላዊ መራራቅ እና ሌሎች የጤና መስፈርቶች APS ለሁሉም ተማሪዎች በአካል የሚሰጥ ትምህርት እንዲጀምሩ በሚያስችል መንገድ ከተስተካከሉ በዚያን ጊዜ የሥራ አፈፃፀማችንን እንደገና እንገመግመዋለን።
- የጤና ሁኔታዎች ቢባባሱ APS ምን ያደርጋል፡ ከ CDC እና ከስቴት እና ከአከባቢ የጤና ባለስልጣናት በየቀኑ የ COVID-19 መመሪያ መከታተል ቀጥለናል። ቅይጥ የትምህርት ቤት ወስጥ ሞዴላችን በስቴቱ የእንደገና መክፈት እቅድ በደረጃ 3 የትምህርት ዓመቱ መጀምር ላይ የተመሠረተ ነው። ከአርሊንግተን ካውንቲ የህዝብ ጤና ክፍል የጤና መረጃ እና የምክረ ሃሳቦች ት/ቤቶችን መዝጋትን አስፈላጊ ካደረጉ በቅይጥ ሞዴሉ ውስጥ የሚሳተፉ ተማሪዎች እና ሰራተኞች አሁን ካለው የሙሉ ጊዜ የርቀት ትምህርት ሞዴል ጋር በይዘት ተመሳሳይ ወደሆነ የሙሉ ጊዜ የርቀት ትምህርት ይሸጋገራሉ ይህም አስተማሪ-መር/በጥምረት የሆነ መመሪያ እና በጥምረት ያልሆነ መመሪያን ቅይጥ ያካትታል።
- የርቀት ትምህርት ከዚህ ካለፈው ፀደይ ምን ያህል የተለየ ይሆናል፡ በሁለቱም ሞዴሎች አዲስ ይዘት እና በቨርጂኒያ የመማር መመዘኛ ደረጃዎች የሚፈለጉ ሁሉም ኮርሶች ይሰጣሉ፣ ሥራ ይታረማሉ፣ መከታተል ይጠየቃል እና ሁሉም ተማሪዎች ከአስተማሪዎች እና የክፍል ጓደኞቻቸው ጋር የበለጠ ተደጋጋሚ ግንኙነት ያገኛሉ። የርቀት ትምህርት በትናንሽ ቡድኖች ወይም እንደ አጠቃላይ ክፍል በጥምረት የሆነ/አስተማሪ-መር ትምህርት እና በጥምረት ያልሆነ/ራስ-መር ትምህርት የሚይዝ ቅይጥ ያካትታል። ሁሉም የርቀት ትምህርት መሳሪያዎችን ማግኘት እንዲችል መሣሪያዎች እና ተያያዥነት ለሁሉም ተማሪዎች እየቀረበ ነው።
- በቅይጡ አማራጭ ውስጥ ላሉ የትምህርት ቤት ውስጥ ቀናት የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ጊዜዎች ምንድናቸው፡ ለቅይጥ ሞዴሉ የትምህርት ጊዜ ከመደበኛ የትምህርት ቀን ጋር ተመሳሳይ ነው ሆኖም በአውቶቡሶች እና የሙቀት ፍተሻዎች ላይ የመራራቅ መስፈርቶች እና የእጅ መታጠብ መስፈርቶች የተጋነነ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ጊዜዎችን ሊፈልጉ ይችላሉ ስለዚህ የትምህርት ቤቱ ቀን ለአንዳንድ የተማሪዎች ቡድን ከወትሮው በተለየ ጊዜ ሊጀምር ወይም ሊያበቃ ይችላል። ለ 2020-21 የተራዘመ የቀን አሠራሮችን በተመለከተ እስካሁን ውሳኔ አልተደረገም። የክፍተኛ ደረጃ የሳምንታዊ መርሃግብር የትምህርቱ ቀን ምን እንደሚመጣ ቅጽበታዊ ፎቶግራፍ እንዲሰጥዎት ቀርቧል።
- APS በሙሉ ጊዜ የርቀት ትምህርት ውስጥ የትምህርት ቤቱን ባህል እና ትስስር እንዴት ይጠብቃል፡ APS ተማሪዎችን እና መምህራንን ከሚመዘገብበት ት/ቤታቸው ለመሰብሰብ ሁሉንም ጥረት ያደርጋል። የመጨረሻዎቹ ቡድኖች እና ምደባዎች በሚገኙ ሰራተኞች እና የተማሪዎች ምዝገባ ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ለምሳሌ አንድ ትምህርት ቤት በምናባዊ መንገድ ለማስተማር የተመረጡ 5 ሠራተኞች ብቻ ቢኖሩት ግን የሙሉ ጊዜ ርቀት ትምህርት ላይ የተመዘገቡ ብዙ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ከሌላው ትምህርት ቤቶች የሚመጡ ሰራተኞች ለተወሰኑ ኮርሶች መመደብ ሊያስፈልግ ይችላል። በነሀሴ መጀመሪያ ላይ የተማሪ ምዝገባ ቁጥሮች እና የሰራተኛ ምርጫዎች ሲኖረን እና ዋና የጊዜ ሰሌዳዎችን እና የተማሪ ቡድኖችን መፍጠር መጀመር ስንችል የበለጠ መረጃ ይገኛል።
የመረጡት ሞዴል ምንም ይሁን ምን ለሁሉም የክፍል ደረጃዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጠንካራ ወደ ትምህርት ቤት መመለስን ለማቅረብ ቁርጠኛ አቋም አለን። የእኛ የስራ ሀይል በደህንነት፣ በልጆች መንከባከቢያ እና መጓጓዣ ላይ ለማተኮር የሚቀጠለው ሰኞ ሐምሌ 13 ቀን ይገናኛል እናም ሀምሌ 14 ላይ ለከተማ አዳራሽ እንዲቀላቀሉን አበረታታዎታለሁ። አመሰግናለሁ።
ከሰላምታ ጋር
Dr. Francisco Durán
የበላይ ተቆጣጣሪ
Arlington Public Schools