APS በመስመር ላይ የተማሪዎችን የሕመም ምልክት ማጣሪያ ሰኞ፤ ማርች 1 ይጀምራል

የአርሊንግተን የህዝብ ትምህርት ቤቶች ከአርሊንግተን ካውንቲ የህዝብ ጤና ክፍል ጋር በመመካከር ለተማሪዎች የመስመር ላይ የሕመም ምልክት ማጣሪያ አዘጋጅተዋል፡፡ APS በአውቶቡስ ማቆሚያዎች እና በት/ቤቶች ከመድረሳቸው በፊት የሰራተኞችን እና የተማሪ ጤናን ቅድመ ማጣሪያ ለማድረግ የኳልትሪክስ (Qualtrics) መድረክን እየተጠቀመ ነው፡፡ የዚህን ምርመራ ሂደት ለማቀላጠፍ፣ አስፈላጊ የጤና መረጃዎችን ለመከታተል እንዲሁም የሰራተኞቻችንን፣ የተማሪዎችን እና የቤተሰቦቻችንን ጤና እና ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳል፡፡ከማርች 1 ቀን ጀምሮ ሁሉም ወላጆች/አሳዳጊዎች ለእያንዳንዱ ተማሪ  የቨርጂኒያ የጤና  መመሪያን በመጠቀም የተሰራውን በየቀኑ የመስመር ላይ የሕመም ምልክት ማጣሪያ ይላክላቸዋል፡፡

ተማሪዎ የርቀት ትምህርትም ይሁን በአካል የሚሳተፈው ዕለታዊ የማጣሪያ እና የተጋላጭነት ጥያቄዎች ለእያንዳንዱ ወላጅ/ሞግዚት በኢሜል እና በ ቴክስት ከሌሊቱ 5፤30 ይላካል፡፡ የጤና ምርመራው በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ በአረብኛ፣ በሞንጎሊያኛ እና በስፓኒሽኛ ይገኛል፡፡ጥያቄዎቹ አንድ ተማሪ አውቶቡሱ ለመሳፈር ወይም ትምህርት ቤት ከመሄዱ በፊት ወይም በትምህርት ቤት-ተኮር እንቅስቃሴዎች ከመሳተፉ በፊት መጠናቀቅ አለባቸው። የሕመም ምልክት ምርመራው በአውቶቡስ ማቆሚያ ወይም ትምህርት ቤት ከመድረሱ በፊት ካልተጠናቀቀ፣ ተማሪው ቀኑን እንዲጀምር ከመፈቀዱ በፊት ከአውቶቡስ ወይም ከትምህርት ቤት አስተናጋጁ ጋር ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል፡፡የጤና ምርመራ ደረጃዎች እና ውጤቶችየማጣሪያ ጥያቄዎችን እና አንድ የእውቅና ማረጋገጫ ቅጽን ያካትታል።

  • የጤና ምርመራ ጥያቄዎችየመጀመሪያው ማያ ገጽ ስለ ትኩሳት ስለ ሳል እና ስለ ሌሎች ከጤንነት ጋር የተዛመዱ ምልክቶች ጥያቄዎችን አዎ ወይም የለም የሚመሉሳቸው ጥያቄዎች የያዘ ይሆናል፤ እንዲሁም ማንኛውንም ሪፖርት የተደረጉ የቅርብ ግንኙነቶች፣ የ COVID ምርመራ ወይም አዎንታዊ ውጤቶችን ያካትታል፡፡ ከታች ያሉት ጥያቄዎች

o በየቋንቋው የምንሞላበት ቦታ

  • ማረጋገጫ ጽ፤ ሁለተኛው ማያ ገጽ የ APS የጤና ቅነሳ ስልቶችን ለማክበር ስምምነት እና ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡

የአርሊንግተን የህዝብ ትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ አባል እንደመሆኔ መጠን ተማሪዬ እና እኔ እንስማማለን፤  በየቋንቋው የምንሞላበት ቦታለሁሉም የጤና ምርመራ ጥያቄዎች የለም መልስ ከሰጡ እና ለእውቅና መስጫ ቅጽ እስማማለሁ” የሚል መልስ ከሰጡ አረንጓዴ ምልክት ያገኛሉ ይህም ተማሪው እንዲገኝ ያስችለዋል፡፡

የማጣሪያውን ውጤት ለአውቶቡስ ወይም ለትምህርት ቤት አስተናጋጅ ያሳዩ፡፡ለማንኛውም የማጣሪያ ጥያቄዎች አዎ የሚል መልስ ከሰጡ ተማሪዎ እንዲገኝ አይፈቀድለትም እና እንዴት መቀጠል እንዳለብዎ ደረጃ በደረጃ መመሪያዎችን የያዘ የቀይ X ተከታይ ኢሜል ይደርስዎታል፡፡

ማጣሪያውን ማጠናቀቅ ያለበት ማን ነው

APS የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ ጤና በተመለከተ የተሟላ እና ትክክለኛ መረጃን ለመያዝ እንዲችል ተማሪዎ በሩቅ ትምህርትም ይሁን በአካል ተገኝቶ ማጣሪያውን እንዲያጠናቅቅ ሁሉንም ቤተሰቦች እንጠይቃለን፡፡ ይህ ማጣሪያ የቅርብ ግንኙነቶችን ለመከታተል እና ሪፖርት ለማድረግ፣ ሪፖርት የተደረጉ አዎንታዊ ጉዳዮችን፣ COVID የመሰሉ ምልክቶችን እና ሌሎች በሽታዎችን ለመከታተል እና በሁሉም የ APS ሰራተኞች እና ተማሪዎች መካከል ተገኝቶ ለመከታተል ያገለግላል፡፡

ሕመም ምልክት ማሳያ ድግግሞሽ

ሥርዓቱ የትምህርት ቀንን ከተጨማሪ እንቅስቃሴዎች መለየት ስለማይችል ሁሉም ቤተሰቦች በየሳምንቱ በየቀኑ መልእክቶች ይደርሳቸዋል፡፡ ቅዳሜና እሁድ በአትሌቲክስ ወይም በሌሎች ትምህርት ቤት-ተኮር እንቅስቃሴዎች ከመሳተፉ በፊት ማጣሪያ በሳምንቱ መጨረሻ መጠናቀቁ አስፈላጊ ነው፡፡

ተጭማሪ መረጃየጤና ማጣሪያ ጥያቄዎችን ሂደት ደረጃ በደረጃ ለመመልከት በእንግሊዘኛ እና ስፓኒሽኛ ማጣሪያ ማስታወቂያውን ይመልከቱ፡፡  የማጣሪያ ሂደት እይታ እና በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQ) በመስመር ላይ ይገኛሉ፡፡