የክትባት አስፈላጊነት ማሳወቂያ

በጋውን በጉጉት እየተጠባበቁ ሳለ ለአዲሱ ለትምህርት ዘመኑ ዝግጁ እንዲሆኑ ለማስቻል የክትባቶችንና የአካላዊ ምርመራዎችን በእቅዶችዎ ውስጥ ማካተትዎን ያረጋግጡ!የቨርጂኒያ ስቴት (የቨርጂኒያ ሕግ § 32.1-46.A.4) በስቴቱ ውስጥ በግል ወይም በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚመዘገቡ ተማሪዎች በሙሉ አሁን ካለው የክትባት ተግባራት ላይ አማካሪ ኮሚቴ (ACIP) ምክሮች ጋር የተጣጣሙ ሆነው እንዲቀጥሉ ይፈልጋል፡፡ ተማሪዎች በአካል ትምህርት ቤት ተገኝተው ለመማር በመጀመሪያ የትምህርት ቀን ዝቅተኛውን የጤና መግቢያ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ በሁሉም የትምህርት ቤት የክትባት መግቢያ መስፈርቶች፣ አጋዥ ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎችንና መመዝገብ ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች መረጃ በቨርጂኒያ የጤና መምሪያ ድህረ ገጽ፡ የትምህርት ቤት መስፈርቶች – ክትባቶች (virginia.gov) ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ለሁሉም አዲስ ለሚመዘገቡ ተማሪዎች እንዲያሟሉ ከሚጠበቁባቸው መስፈርቶች በተጨማሪ፡

  • ወደ መዋእለ ሕጻናትና አንደኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች የሄፐታይተስ ክትባት (HAV) የተከፋፈሉ ሁለት ክትባቶችን በትክክል ስለመከተባቸው የሚያሳይ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የመጀመሪያው ክትባት በ 12 ወር ወይም ከዚያ በላይ በሆነ እድሜ መሰጠት አለበት፡፡
  • 7 ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች አንድ ቴታነስ ዲፍቴሪያና ፐርቱሲስ ክትባት (Tdap) ማበረታቻ በ 7 አመት ወይም ከዚያ በኋላ የሚሰጥ ሲሆን እንዲሁም በ 10 አመት ወይም ከዚያ በኋላ የሚሰጠው የማኒንጎኮካል ኮንጁጌት ክትባት (MenACWY) የመጀመሪያ ክትባት ስለመውሰዳቸው ማስረጃ እንዲያቀርቡ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የቨርጂኒያ የጤና ጥበቃ መምሪያ እንዲሁ ለሁሉም የ 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ሂውማን ፓፒሎማቫይረስ (HPV) የመጀመሪያ ክትባት እዲወስዱ ይፈልጋል፡፡ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ልጁ የ HPV ክትባት እንዳይወስድ ከመረጠ ወይም እንደወሰደ ማረጋገጫ ካቀረበ ተማሪው እንዳይካተት አይደረግም፡፡
  • 12 ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች የ MenACWY ክትባት በ 11 አመት እድሜ ላይ ቢከተቡም እንኳ እድሜያቸው 16 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆናቸው የሚኒንጎኮካል ኮንጁጌት ክትባት (MenACWY) የሚሰጠውን የማበረታቻ ክትባት ስለመውሰዳቸው ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተማሪዎች በግል ስለሚኖራቸው መስፈርቶች ወይም ለተማሪው አስፈላጊውን ክትባቶች በአርሊንግተን ካውንቲ የክትባት ክሊኒክ እንዲወስድ ቀጠሮ ለመያዝ ለሚፈልጉ፣ በሚኖራቸው ማናቸውም ጥያቄዎች ላይ እባክዎ የትምህርት ቤት ጤና ክሊኒክ ሰራተኞችን ያግኙ፡፡