የትምህርት ቤት ምግብ ዋጋዎችና የበጋ ትምህርት ቤት ምግቦች ወቅታዊ መረጃ

ከመጋቢት 2022 ጀምሮ፣ ያለ ምንም ወጪ ምግብ ለማቅረብ የብሔራዊ ትምህርት ቤት ምሳ ፕሮግራምን ለማራዘም ኮንግረሱ USDA (የዩናይትድ ስቴትስ የግብርና መምሪያ) ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ የ APS የበጋ ትምህርት በሐምሌ 5 በሚጀመር ጊዜ የትመህርት ቤት የምገባ ፕሮግራሞች ወደ መደበኛ ስራቸው የሚመለሱ ይሆናል፡፡ በዋናነት የተለወጠው ነገር ለሁሉም ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምሳና ቁርስ ምንም ወጪ ሳይኖር በቀጥታ መቅረብ መቆሙ ነው፡፡ተማሪዎ በዋሽንግተን-ሊበርቲ፣ ዶሮቲ ሃም፣ ኢስኩዌላ ኪይ፣ ጀምስታውን ወይም አቢንግዶን የበጋ ትምህርት በመከታተል ላይ ከሆነ፣ በበጋ ትምህርት ቤት ነጻ ምግብ ለማግኘት ብቁ ለመሆን እስከ ሰኔ 30 ድረስ በፋይሉ ላይ የምሳ ማመልከቻ ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡በካርሊን ስፕሪንግስ፣ ራንዶልፍና ባሬት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የበጋ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ነጻ ምግብ የሚያገኙ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱም እነዚህ ትምህርት ቤቶች ለማህበረሰብ አቅርቦት ብቁነት (CEP) ላይ ብቁ በመሆናቸው ናቸው፡፡ CEP ለተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ለነጻ ወይም ለቅናሽ ምግብ ብቁ ከሚሆኑ ተማሪዎች ብዛት መቶኛ ላይ መሰረት በማድረግ ነጻ ምግብ እንዲያቀርቡ ይፈቅዳል፡፡የበጋ ምግብ የመውሰጃ መርሃ ግብር   ካርሊን ስፕሪንግስ፣ ራንዶልፍና ባሬት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በበጋው ትምህርት ክፍለ ጊዜ የምግብ ማሰራጫ ማእከላት ሆነው ያገለግላሉ፡፡ እድሜአቸው ከ 18 እና ከዚያ በታች የሆኑ ተማሪዎች በሙሉ ከ 11 ኤ.ኤም. – 12 ፒ.ኤም. ነጻ ቁርስና ምሳ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ወላጆችና እንክብካቤ አድራጊዎች ለተማሪዎች ምግብ እንዲያነሱ ይፈቀድላቸዋል፡፡ለበጋ ትምህርት ቤትና ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን የምግብ ዋጋ

  • የበጋ ትምህርት ቤት፡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ቁርስ $1.75፣ የመጀመሪያ ደረጃ ምሳ $ 3.05፣ ሁለተኛ ደረጃ $3.15
  • 2022-23 የትምህርት ዘመን፡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ቁርስ $1.80፣ የመጀመሪያ ደረጃ ምሳ $ 3.10፣ ሁለተኛ ደረጃ $3.20
  • ባርክሮፍት፣ ባሬት፣ ካርሊን ስፕሪንግስ፣ ዶ/ር ቻርልስ አር ድሪው እና ራንዶልፍ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች የ CEP ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ያለምንም ክፍያ ምግብ ያቀርባሉ፡፡